colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

የገብርኤል ድምፅ ተሰማ

ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ ሐርና ወርቁን ስታስማማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ /፪/ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ ተሰማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ ውሃ ስትቀጂ ክንፉን እያማታ ሊያበሥርሽ የመጣው በታለቅ ደስታ ከሞገስሽ ብዛት ሲታጠቅ ሲፈታ አቅርቦልሽ ነበር የክብር ሰላምታ ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ ሐርና ወርቁን ስታስማማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ /፪/ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ ተሰማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ የምስራቹን ቃል ምስጢር ተሸክሞ ገብርኤል ተላከ ሊያረጋጋት ደግሞ እርጋታ ተመልታ ነገሩን መርምራ የመልአኩን ብሥራት ሰማችው በተራ ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ ሐርና ወርቁን ስታስማማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ /፪/ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ ተሰማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ እኔ በኅሊና በሥጋም ንጹሕ ነኝ የዚህ ዓለም ፀባይ ኃጢአት የማይነካኝ ሃሳቤ አምላኬ ነው ኑሮዬ በመቅደስ ወንድ አላውቅም እኔ እስከመቼም ድረስ ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ ሐርና ወርቁን ስታስማማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ /፪/ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ ተሰማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ ይደሰታል እንጂ መንፈሴ በአምላኬ በምሥጋና ሳድር ዘወትር ተንበርክኬ ሃሳቤ ለቅጽበት ሌላ መች ያስባል ለኔ ልጅን መውለድ እንዴት ይቻለኛል ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ ሐርና ወርቁን ስታስማማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ /፪/ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ ተሰማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ ከአንቺ የሚወለደው ንዑድ ነው ክብር የተመሰገነ በሰማይ በምድር ምሥጢሩ ኃያል ነው ይረቃል ይሰፋል ከአንቺ በቀር ይህን ማን ይሸከመዋል ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ ሐርና ወርቁን ስታስማማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ /፪/ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ ተሰማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ እፁብ ነው ግሩም ነው አንችን የፈጠረ አንቺን በመምረጡ ሰውን አከበረ ዓለም ይባረካል በማኅፀንሽ ፍሬ ክብርሽን አልዘልቅም ዘርዝሬ ዘርዝሬ ሰላም ለኪ እያለ ሰላም ለኪ እያለ ሐርና ወርቁን ስታስማማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ /፪/ የመልአኩ ድምፅ ተሰማ ተሰማ የገብርኤል ድምፅ ተሰማ