colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ይበራል በክንፉ

ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው /፪/ ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ እንዳልደናቀፍ ጉድባዎችን ሞልቶ ዛሬ ላለሁብት ብርቱ ጉልበት ሆነኝ ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው /፪/ በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ አለሁ እሰከዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ የሕይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከርሱ ጋራ ተፅፏል በልቤ የሚካኤል ሥራ ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው /፪/ በዙሪያዬ ተክሎ የእሳት ምሰሶውን ፅድቅ እየመገበ አሳደገኝ ልጁን የአምላኬን ምሥጋና ዘወትር እያስጠናኝ እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው /፪/ ፊት ለፊት ተተክሎ ከትንሿ መንደር ይሰማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር ይወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ ታላቁን በረከት በውስጤ አፈሰሰ ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከእኔ ጋር ነው /፪/ ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ መራኝ ወደ ሕይወት መዳኔን ወደደ የአሞንን ቋንቋ ከአፌ ላይ አጥፍቶ በጸጋው ቃል ቃኘኝ በበረከት ሞልቶ