በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ /፪/ እግዚአብሔርን በሉት ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው/፪/ ሰማያትን በስንዝር የምትለካቸው--ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው ቀላያትን በእፍኝ የምትሰፍራቸው ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው ቃልን ብቻ ልከህ የምታሰማመር ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በድንቅ አሰራርህ ግሩም ነህ እግዚአብሔር ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ /፪/ እግዚአብሔርን በሉት ስራህ ግሩም ድንቅ ነው/፪/ ለእኔ የዋልክልኝ መቼ የሚረሳ ነው-ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው ከሰው መቆጠሬ ጌታዬ በአንተ ነው ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በላዬ ዘርግተህ የክብርን ደመና ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው ቅጥሩን አዘለልከኝ ድጋፍ ሆንከኝና ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ /፪/ እግዚአብሔርን በሉት ስራህ ግሩም ድንቅ ነው/፪/ እሰግድልሃለሁ ፊትህ ተንበርክኬ---ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው ውለታህ ማርኮኛል እግዚአብሔር አምላኬ ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው ከአንተ ጋራ ሆኜ ምን ይጎድልብኛል ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በምህረትህ ጎብኘኝ ፀጋህ ይበቃኛል ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በልዎ ለእግዚአብሔር ግሩም ግብርከ /፪/ እግዚአብሔርን በሉት ስራህ ግሩም ድንቅ ነው/፪/ ስለኃጢያቴ ብዛት ሊወግሩኝ ሲነሱ--ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው በፊቱ አቁመውኝ ሲከሱኝ በብዙ ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው ጥፋቴን አይሻም እርሱ መች ፈረደ ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው ውለታው ግሩም ነው ሊምረኝ ወደደ ሥራህ ግሩም ድንቅ ነው