እልል በሉ መጣ ሙሽራው ደስ ይበለን እግዚአብሔር አድርጓል መልካሙን ነገር ለሁላችን ዘይቱን ሙሉት መብራቱም ይብራ -- መጣ ሙሽራው ተወዳጁ ሰው መጣ ሙሽራው--- ደስ ይበለን በፊቱ ቁሙ ቆነጃጅቱ --- መጣ ሙሽራው የፍቅር ግብዣው ደርሷል ሠዓቱ -- ደስ ይበለን በልዩ ግርማ ተውቧል ዛሬ ----መጣ ሙሽራው አዲስ ምስጋና ታላቅ ዝማሬ ---- ደስ ይበለን እንደወደደ አድርጓል ጌታ --- መጣ ሙሽራው ማን ይገልጸዋል የእርሱን ውለታ --- ደስ ይበልን በልጆቹ ቤት በክብር ነግሷል ---መጣ ሙሽራው በነገር ሁሉ ራስ ሆኗቸዋል --- ደስ ይበለን ይህን ያለውን በጊዜው ሰራ ----መጣ ሙሽራው ይሄው ቆመዋል በክብር ስፍራ -- ደስ ይበለን