ተክለ ሃይማኖት ባህታዊ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ በአደባባዩ ተተክለሃል ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል ቃልኪዳን አለ የገነነ ምህረት የሚያሰጥ የታመነ በስምህ ውሃ አጠጥተን ዋጋችን በዝቷል አባታችን ተክለ ሃይማኖት ባህታዊ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ በአደባባዩ ተተክለሃል ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል እኛም ሆነናል ልጆችህ ማርኮ አስቀርቶን ምግባርህ በምልጃ ጸሎት ትሩፋት ቤታችን መላ በረከት ተክለ ሃይማኖት ባህታዊ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ በአደባባዩ ተተክለሃል ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል ምህረት ይዘንባል ከሰማይ በአንድ እግርህ ቆመህ ስትጸልይ ብዙ ተጋድለህ አትርፈሃል ያገለገልከው አክብሮሃል ተክለ ሃይማኖት ባህታዊ ምድራዊ ሲሉህ ሰማያዊ በአደባባዩ ተተክለሃል ተክልዬ መልካሙን ፍሬ አፍርተሃል ተሰባበሩ ጣኦታቱ አምነው ሰገዱ መኳንንቱ የበረታው ቃል ከአፍ ወጥቶ የአምላክ አድርጎሃል ሁሉ ገዝቶ