አዳምን ያልተወው እንደ ተሰደደ እሰይ የምሥራች ዛሬ ተወለደ ፪ አምላካችን መድኃኒታችን ተወለደ ለነፃነታችን ፪ አዳምን ያልተወው እንደ ተጨነቀ እሰይ የምሥራች ዛሬ ተጠመቀ ፪ አምላካችን መድኃኒታችን ተጠመቀ ለነፃነታችን ፪ አዳምን ሊጠራ የመጣው ሙሽራ በገሊላ መንደር ለሠርግ ተጠራ ፪ አምላካችን መድኃኒታችን ተጠመቀ ለነፃነታችን ፪ ሠርግ ቤት እንዳለ በክብር ተቀምጦ የወይን ጠጅ ሆነ ውሀው ተለውጦ፪ አምላካችን መድኃኒታችን ተጠመቀ ለነፃነታችን ፪ እጅግ ያስደንቃል የጌታችን ሥራ ፪ በገሊላ መንደር ይህን ተአምር ሠራ