ነዓ /፬/ በልዑል የጌታ ባለሟል ቅዱስ ሚካኤል ሰይጣን ስልጣን ሲሻ አምላክን ለመሆን ተለየ ከክብሩ ወርዶ ከሥልጣን በታማኝነት ህ ጸንተህ በመቆምህ በመላእክት ላይ ልዑል አደረገህ ነዓ /፬/ በልዑል የጌታ ባለሟል ቅዱስ ሚካኤል እስራኤላውያን በሙሴ ሲመሩ ጽኑ አደረካቸው ክፉን እንዳይፈሩ በአንተ ረዳትነት ተከፍሎ ባሕሩ እነርሱም በአንድነት ሄዱ ተሻገሩ ነዓ/፬/ በልዑል የጌታ ባለሟል ቅዱስ ሚካኤል ባሕራን የዋሁ ሰው የሞት ጥሪ ይዞ ወደ አጥፊዎች ሀገር እያለ በጉዞ በሰው ተመስለህ ፈጥነህ ደርሰህለት የሞቱን ድብዳቤ በሕይወት ለወጥክለት ነዓ/፬/ በልዑል የጌታ ባለሟል ቅዱስ ሚካኤል የአፎም ያ አባት አጽናኝ አለኝታዋ ረዳቷ ነበረ ምስልህ ጠባቂዋ በአንተ ተመስሎ ሰይጣን ሲፈትናት በሚያስፈራው ግርማህ ፈጥነህ ደረስክላት ነዓ/፬/ በልዑል የጌታ ባለሟል ቅዱስ ሚካኤል