ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ማነው ብዬ ጠየኩ በረከት ፈልጌ ልሳለመው ናፈኩ ክብሩን ልመሰክር ተፈታ ምላሴ ከደጁ ደርሼ ፍቅሩን በመቅመሴ በኢትሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ ተለይህ ለአምላክ ዓለምን ጥለህ ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር ስለ አንተ ዝና ስለ አንተ ክበር ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ አክባሪው አምላክ ስላከበረህ ዛሬም ከእኛ ጋር በመንፈስ አለህ እጅ እንነሳለን በትህትና የጻድቅ ፀሎት ሀይል አላትና ተክለሃይማኖት ፀሀይ ፀጋ ይምጣልኝ ከሰማይ ወደ ለምለም መስክ ስበኸ መራኸን የቃሉን ወተት አጠጥተኸን ያቀጣጠልከው የወንጌል ችቦ የአምላክ አድርጓል ትውልዱን ስቦ ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ቤቴ ደጄ ሰላሳ ስልሳ መቶ ያፈራህ በደብረ አስቦ ቆህ በአንድ እግርህ የመቶሎሚ መሻት ቀረና የጌታ መንገድ ጥርጊያውም ቀና ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ በኢትሳ ምድር ዘር ሆነህ በቅለህ ተለይህ ለአምላክ ዓለም ጥለህ ደብረ ሊባኖስ ህያው ምስክር ስለአንተ ዝና ስለአንተ ክብር ተክለሃይማኖት ወዳጄ ተባርኳል በአንተ ጓዳ ደጄ