እይራየኒ አይነሙት ወይርከበኒ ኩነኔ ነፍሴን አደራ በሰማይ/2/ ተክልዬ ፀሃይ ፅላሌ ዞረሪ ነይ መስክሪ የተክለሃይማኖትን ዝና አውሪ የእንቁርቁሪት ጸበል ማር ወተት ሁሉም ተፈወሱ ሲጠጡት/2/ ትህትናህ ግሩም ነው ቅድስናህ ሀይቅ እስጢፋኖስ አገልግለህ ደብረ ዳሞ ዘልቀህ ክንፍ አወጣህ ደብረ ሊባኖስ ላይ አርፏል አፅምህ/2/ ፈተታና ዳሞት ተሻግረህ ባርያንን ሁሉ አሳፈርክ በንብ ቀፎ አርገው ቢጥሉህ ሚካኤል በክንፉ አቀፈህ/2/ በደብረ አሰቦት ጦር ተክለህ 29 ዘመን ተጋድለህ ወዝህ ያረፈበት ነጠብጣቡ ድውይ ይፈውሳል ቃል ኪዳኑ/2/ ይህን ሁሉ ጸጋ ተችረሃል ቁጥርህ ከመላዕክት ተስተካክሏል አባቴ/2/ እኔ ስልህ ነፍሴን ታደግልኝ በምልጃህ/2/