ፈጥነህ ቅረበን ጊዮርጊስ/2/ ለአምላክህ የታመንክ እስከ ሞት አክሊልን አገኘህ ፍጡነ ረድኤት መከራን ታገሰ በወጣትነቱ ስለጌታው ፍቅር ጊዮርጊስ ሰማዕቱ የረገጥክባቸው የእግሮችህ ፋና ይመሰክራሉ ጊዮርጊስ የአንተን ዝና በመከራው ጸና ሩጫውን ፈፀመ የህይወትን አክሊል ጊዮርጊስ ተሸለመ ሥጋውን ለመጋዝ ነፍሱን ለአምላክ ሰጥቶ ተጋድሎ አሸነፈ በእምነቱ ፀንቶ ስለጌታው ፍቅር ጊዮርጊስ መች አፈረ እኔ ክርስተያን ነኝ ብሎ መሰከረ ኢየሱስ ክርስቶስ አብዝቶለት ፀጋ ለነፍሱ ተገዛ ሳይሳሳ ለስጋ ሀያሉ ጊዮርጊስ የልዳው ጋናና ከጠላት አድነን ፈጥነህ ድረስና አውሬው በዙሪያችን ሊውጠን ሲያደባ ስም ጋሻ ሆነን መከለያ አንባ