ጋሻውን ይዞ በፈረስ አቤት ማማሩ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤሩታዊትን አዳናት ዘንዶ እንዳይበላት ደራጎን፨፪፨ ጋሻውን ይዞ በወጣትነቱ ጋሻውን ይዞ ፅድቅን ለይቶ አውቆ ጋሻውን ይዞ ለዘመቻ ወጣ ጋሻውን ይዞ ጋሻ ጦሩን ታጥቆ ጋሻውን ይዞ በህጻንነቱ ጋሻውን ይዞ በአምላኩ ተጠርቶ ጋሻውን ይዞ ድል ነሣ ጠላቱን ጋሻውን ይዞ ጥበብን ተሞልቶ ጋሻውን ይዞ ሀያሉ ጊዮርጊስ ጋሻውን ይዞ የፅድቅ ወታደር ጋሻውን ይዞ በተጋድሎው ጸና ጋሻውን ይዞ በአምላኩ ሳያፍር ጋሻውን ይዞ አራት ሞትን ሞተ ጋሻውን ይዞ ለስጋው ሳይሳሳ ጋሻውን ይዞ ለአምላኩ ክብር ጋሻውን ይዞ ተቀበለ አበሳ ጋሻውን ይዞ የልዳው ንጉስ ጋሻውን ይዞ ቅዱሱ አንበሳ