colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

አቤቱ አንተን እጠራለሁ

አቤቱ አንተን እጠራለሁ ነፍሴን ወዳንተ አነሳለሁ ዝም አትበለኝ እጮሀለሁ (2) የሐጢያት ሸክሙም ከብዶኛል የሥጋ ወጥመድም አስሮኛል የሰይጣን ሽላግ አጥቅቶኛል (2) ደካማ ነኝ በጣም ችግረኛ ምስኪን ተስፋ-ቢስ አመጸኛ ከመንጋው የራቅኩኝ ብቸኛ (2) ሐጢያቴን ሁሉ ይቅር በለኝ የንስሀን በር ክፈትልኝ መጣሁኝ ጌታ ተቀበለኝ (2) የቤትህ ናፍቆት አቃጠለኝ የቃልህ በረከት ራበኝ እባክህ ጌታ ይቅር በለኝ (2) ከአንተ ኮብልዬ ተንከራተትኩ ምንም ላይረባኝ ከንቱ ባከንኩ ለበስባሽ ሥጋዬ ተገዛሁ (2)