ቤተ ክርስቲያንን አንተዉም ከቶ የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ የአምላካችንን ቤት አንተዉም ከቶ ሁሉንም በሁሉ ለሚሞላው ጌታ ሙሽራው የሆነች ቤቱ ተሰኝታ በክብር በሞገስ በጸጋ ተሞልታ ደምቃ ትኖራለች ለዓለም አብርታ(፪) ዲያብሎስ ቢጨርስ ቀስቶቹን በሙሉ ወጥመድ ቢዘረጋ በጒዟችን ሁሉ እንሻገራለን የአምላክን ስም ጠርተን አንዳች አይነካንም እርሱን ተጠግተን(፪) በስሙ መሰብሰብ በስሙ መስራት ስለ ስሙ መኖር በስሙ መሞት ጠላት ዲያብሎስን ምን ባያስደስት ይህ ነው ክርስትና ይሄ ነው ህይዎት(፪) ከትዉልድ ለትዉልድ የምናስረክበው ለልጅ ልጅ አዉርሰን ደስ የምንሰኘው አይደል ብርና ወርቅ አይደል ሌላ ሀብት ሐይማኖታችን ነው የእኛ እርስት ጉልት(፪)