ያሬድ ማኅሌታይ ለእግዚአብሔር ካህኑ ስብሐተ ትንሳኤ ዘይዜኑ ኦሪት ቶታኑ ወወንጌል አሣዕኑ/፪/ ትርድአነ ነዓ መካኑ/ሀበ ዝ መካን/ ከመፀበል ፀርነ ይኩኑ/፪/ ትርጉም:- የእግዚአብሔር ካህን ያሬድ ወንጌል ጫማው: ኦሪት የጫማው ማሰሪያ ነው:: ቅዱስ ያሬድ ሆይ ትረዳን ዘንድ ከዚህ ቦታ /ቤተ መቅደስ/ ና: በመምጣትህም ጠላቶቻችን እንደ ትቢያ ይሁኑ/በነው ይጥፉ/።