አስራ ሁለቱ ሐዋርያት ምንኛ እድለኞች ናቸው(፪) ጸጋ መንፈስ ቅዱስ በጽዮን አዳራሽ የወረደላቸው(፪) ዞረው እንዲያስተምሩ በየምድባቸው(፪) ሰባ ሁለት ቋንቋ (፪) ተገለጸላቸው(፪) ጴጥሮስ ሲጠባበቅ ያንን የተስፋ ቃል(፪) ወርዶ አጥለቀለቀው(፪) የመንፈስ ማዕበል(፪) ደቀ መዛሙርት በመንፈስ ሲሞሉ(፪) ጉሽ ጠላ ነው ብለው (፪) አይሁድ አሳበሉ(፪) በመንፈስ መሪነት ጽድቅን የሚመኙ(፪) ሦስት ሺ አማኞች (፪) በአንድ ቀን ተገኙ(፪) እንደባረካቸው ሐዋርያትኝ(፪) አቤቱኝ ጌጣ ሆይ(፪)እናኝም ባርከን (፪)