እዉቀት ጥበብ የምገበይባት(፪) ሰንበት ትምህርት ቤቴን አምላክ ይጠብቃት እዉቀት ጥበብ የምገበይባት አሳድጋኛለች በማር በወተት እቅፍ ድግፍ አድርጋ እንደ እናት አባት በቅዱስ ሚካኤል ምልጃ እና ጸሎት ይሄው ደርሻለሁ ለዛሬዋ እለት ምሥጢረ ስላሴ የእምነቴን መሰረት ከአባቶች ተምሬ የተረዳሁባት ምግባር ከሃይማኖት ትዉፊት ያወቅሁባት የእዉቀት ገብያ ጽርሀ ጽዮን ናት የአለሙ ሞገድ ሲበዛ ፈተና እስከ መጨረሻው በእምነት እንድንጸና የመላእክት አለቃ በምልጃህ ቶሎ ና እኛ ስጋዊያን ደካሞች ነንና በክንፎች ጋርደን ቅዱስ ሚካኤል ምልጃህ አይለየን ከእኛ ከሁላችን ማኅበራችንን ጠብቅ ለዘላለም ልጆችህ እንኑር በፍቅር በሰላም