መስቀሉን ተሸክመን በእምነት እንራመድ ለሰማያዊው ክብር እንጓዝ (2) ወደእርሱ ዘንድ እግዚአብሔር አብ ላከ አንድያ ልጁን /2/ እርሱ ወዷልና እንዲሁ ዓለሙን/2/ አዝ . . . ከኃጢያት ያዳንከን ደምህን አፍስሰህ /2/ የሰላም ባለቤት አምላክ አንተ ነህ /2/ አዝ . . . ይቅር ባይ መሐሪ ሰው ወዳጅ አምላክ /2/ በመንፈስህ አጽናን እንዳንወክ /2/ አዝ . . . አንተ ነህ ሕይወት መንገድና እውነት/2/ አብቃን የእኛ ጌ ለዘላለም ሕይወት /2/ አዝ . . .