ሚካኤል ሊቀ መላእክት /፪/ አንተ አድነን እኽ አንተ አድነን ከክፉ መዓት እስኪ ላመስግንህ የጌታ ባለሟል ክብር የተሰጠህ ነህ ከቸሩ እግዚአብሔር ታምሩ መብዛቱ ባማላጅነቱ ለምስኪኖች ደራሽ መድኃኒት ነው ፈዋሽ ሚካኤል ሚካኤል ሊቀ መላእክት /፪/ አንተ አድነን እኽ አንተ አድነን ከክፉ መዓት ዛሬም እንደ ቀድሞ እንደነ አፎሚያ እኛንም ጠብቀን ከክፉ መከራ በአማላጅነጥ ዘውትር ሲማጸኑ ፈጥነህ ትደርሳለህ ልታድናቸው ሚካኤል ሚካኤል ሊቀ መላእክት /፪/ አንተ አድነን እኽ አንተ አድነን ከክፉ መዓት ስምህን ለሚጠሩህ ዝክርህን ለዘከሩ ዋስ ጠበቃቸው ነህ አ ንተን ለሚያከብሩ ጸበልህ ፈዋሽ ነው በእምነት ለቀረቡት ጥበቃህ አይለየን ሚካሌል ሆይ እርዳን ሚካኤል ሚካኤል እኽ አንተ አድነን ከክፉ መዓት/፪/