colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ድንግል ትንሳኤሽን

ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት(2) ሞትን የረገጠው ልጅሽ ካንቺ ጋር ነው ውጦ የሚያስቀርሽ የቱ መቃብር ነው የዕርገትሽን ዜና ከቶማስ ሰምተናል ትንሳኤሽ እውነት ነው ሰበንሽን አይተናል ---ሞትማ በሞት ተሸንፏል-- ባንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል(2)- ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት(2) ልናየው ወደድን የቶማስን ክብር ለምን ተሰወረን የትንሳኤው ምስጢር በራችንን ዘግተን በጸሎት ወድቀናል ተገልጠሽ አብሪልን ልጆችሽ ናፍቀናል ---ሞትማ በሞት ተሸንፏል-- ባንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል(2) ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት(2) መዝሙረኛው አባትሽ ዳዊት ጽፎልናል ሞትን የማያይ ሰው ማን አለ ብሎናል ይህ እውነት በዘመን ባንቺ ላይ ቢደርስም በሞት ተሸንፈሽ መቃብር አትወርጂም ---ሞትማ በሞት ተሸንፏል-- ባንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል(2)- ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት(2) ቶማስ ከደመናው ወርዶ ሲያናግረን ስለሆነው ነገር እጅጉን ተመሰጥን እኛም ይህን ክብር ተመኘን ለማየት ድንግል አሳስቢልን ኪዳነምሕረት ---ሞትማ በሞት ተሸንፏል-- ባንቺ ላይ እንዴት ሀይል ያገኛል(2)- ድንግል ትንሳኤሽን እስከምናይ ድረስ ገብተናል ሱባኤ ባንድነት በመንፈስ ለኛ እስከሚገለጥ ቶማስ ያየው እውነት አንወጣም ከደጅሽ ኪዳነምህረት(2)