ፍቅርህ ማረከኝ በሕይወቴ በዘመኔ(2) እግዚአብሔር ለኔ መድኃኒቴ ፍቅርህ ማረከኝ በሕይወቴ በዘመኔ ተገዝቻለሁ በወርቅ ደምህ ዓለምን ትቼ ላገለግልህ ሞትህ ህይወቴ ለኔ ሆኖኛል ባንተ መከራ ሸክሜ እርቅዋል ለክብርህ ቆሜ እዘምራለሁ እንደ አቅሜ አገንሃለሁ(2) አዝ ምድር እና ሰማይ እልል ይበሉ ምስጋና ላንተ ይድረስ እያሉ መሳይ የለህም ለቅድስና አቀርባለሁ ላንተ ምስጋና ጣቴ በገና ይደረድራል በቀን በሌሊት ያመሰግናል(2) አዝ ክብርህን አይተው ጠላቶች ፈሩ ለጌትነትህ ወድቀው ተገዙ እንዲ ነህ አምላክ እንዲ ነህ ጌታ ሁሉን በፍቅር የምትረታ ባንተ ተመካን በፈጣሪያችን አዳኝ በሆንከው በንጉሣችን(2) አዝ