የመስቀሉ ፍቅር ፍቅር ሲገባን (4) እመቤታችንን እናያታለን(2) የመስቀሉ ፍቅር የገባቸው (4) እመቤታችን አለች ከጎናችው(2) አባ ሕርያቆስ አባታችን የመስቀሉ ነገር ሲገባው ልቤ አፈለቀ አለ መልካም ነገር ከእመቤታችን ጋር ስነጋገር ከድንግል ማርያም ጋረ ስነጋገር አዝ ለመናኔው ጸሎት ልዩ ዕጣን የዋሻው ሻማ ነሽ እመብርሃን መዓዛሽ ሸተተኝ ከግሸን ትናፍቂኛለሽ ምን ልሁን ትርቢኝምአለሽ ምን ልሁን አዝ አዝ ዳዊት በመዝሙሩ ያነሳሳሻል ያዕቆብ ድንኳን ነሽ ይልሻል የእግዚአበሔር ሀገር የሚሉሽ እመቤቴ ማርያም አንቺ ነሽ (2) አዝ ቤተ ልሔም ስሄድ አይሻለሁ ቀራንዮ ስሄድ አይሻለሁ ፍጹም አትለዪም ከልጅሽ ያንችስ ልዩ ነው ፍቅርሽ (2) አዝ ለመናኒው ጸሎት ልዩ ዕጣን የዋሻው ሻማ ነሽ እመብርሃን መዓዛሽ ሸተተኝ ከግሸን ትናፍቂኛለሽ ምን ልሁን ትርቢኝም አለሽ ምን ልሁን አዝ