ሕይወቴ ቢመራ ጌታ በቃልህ ጣፋጭ ይሆን ነበር ሲያድሰኝ ፍቅርህ የአንተ ጸጋ ጌታ ስለበዛልኝ ጨለማው ተገፎ ብርሃንህ መራኝ በሕይወቴ በዘመኔ ደስ የሚለኝ ለኔ በወንጌል ማመኔ ወዴት እሄዳለሁ የእጅህ ጥበብ ሆኜ ፍቅርህ እያደሰኝ ሞተህልኝ ድኜ ምን ዓይነት መውደድ ነው ለኔ አንተ ያለህ ምን ይከፈልሃል ለፍጹሙ ፍቅርህ አዝ… ምን ዓይነት መውደድ ነው አንተ ለእኔ ያለህ ምን ይከፈለዋል ለፍጹሙ ፍቅርህ ደጅህ ላይ ተጥዬ ደጅህ ላይ ልሙት ቃልህን ልጠብቅ በፍፁም ፍርሃት አዝ…