colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ

ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ በአካለ ሥጋና በአካለ ነፍስ /፪/ ያሉ ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ የእግዚአብሔር ዐይኖቹ ጻድቃንን ከማየት ጆሮቹም አይርቁም እነርሱን ከመስማት የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደርጋለች በምልጃቸው እንመን አናመንታ በአንዳች ጊዜያዊ ፈተና ሳያሰቅቃቸው እሳትና ስለት ሳያስፈራራቸው ሰማያዊው ተስፋ ስለሚታያቸው በመከራ ሁሉ ጸኑ በእምነታቸው ኃጥኡ ነዌ እንኳ በሲዖል እያለ ስለ ወንድሞቹ ምሕረት ከለመነ እናንተማ ጻድቃን በገነት ያላችሁ ምንኛ ትረዱን አምነን ስንጠራችሁ ቀዝቃዛ ውሃ እንኳን በጻድቅ ሰው ስም የሚያጠጣ ቢኖር ዋጋው አይጠፋም ብሎ እንዳስተማረን ጌታ በወንጌል አምነን እንፈጽመው ዋጋ ያሰጣል