colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ላመስግንህ የኔ ጌታ

ላመስግንህ የኔ ጌታ ላመስግንህ ልቀኝልህ የኔ ጌታ ልቀኝልህ ህይወቴ ነው ዝማሬዬ ትሩፋቴ የሰጠኸኝ እንዳከብርህ አንተ አባቴ (2) ከኔ ሆነህ የምሰጥህ ባይኖረኝም ከሰጠኸኝ የአንተን መስጠት አይከብደኝም ጥበቤ ነህ የምስጋና መሰረቴ ዝማሬዬን ያፈሰስከው በህይወቴ አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና(2) አዝ ባዶ እኮ ነኝ የኔ ጌታ ምን ልቅዳልህ በእጄ ላይ አንዳች የለኝ የምሰጥህ ላንተ ክብር የሚመጥን ህይወት የለኝ ዝማሬዬን በቸርነት ተቀበለኝ አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና(2) አዝ ከምድር ላይ ከአፈር ስትፈጥረኝ ከምስጋና የተለየ ምን ስራ አለኝ ቀንና ሌት በመቅደስህ እቆማለሁ አምላኬ ሆይ ሳወድስህ እኖራለሁ አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና(2) አዝ እዝራ ስጠኝ የከበረ መሰንቆህን ዳዊት ስጠኝ የሚፈውስ በገናህን መዝሙር ቅኔ ተምሪያለሁ ከአባቶቼ እዘምራለሁ ባንተ ፍቅር ተነክቼ አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና አዝ