እኔ እወድሃለሁ መድኃኒቴ መታመኛዬ ነህና ረዳቴ መታመኛዬ/፪ መመኪያዬ አንተ ነህ የሕይወቴ ተስፋ ጌታ ሆይ ጠብቀኝ ከሰይጣን ዘለፋ አዝ አቤቱ ጌታ ሆይ በስምህ አድነኝ ጩኸቴንም አድምጥ ጸሎቴንም ስማኝ አዝ የነፍሴ መዳኛ የአጥንቴም ሕይወቱ ወልደ አብ ክርስቶስ አንተ ነህ በእውነቱ አዝ ከአንተ ተለይቼ እንዳልጠፋብህ የቀናውን መንገድ ይምራኝ መንፈስህ አዝ ወደኔ ተመከት ነፍሴንም አድናት እንደቸርነጥ ሠውረኝ ከኃጢያት አዝ ወደዓለም ስትመጣ በግርማ በክብር ጌታ ሆይ አስበኝ ወድቄ እንዳልቀር አዝ