ሚካኤል ኃያል ሚካኤል ከጠላታችን ነፃ አወጣን ከአምላክ ተልኮ እረዳን፤ (2) ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና መርተህ አወጣኸን ከግብፅ መከራ የእግዚአብሔር መልአክ ርኅሩህ ሚካኤል ሆይ ናና ዛሬም ታደገኝ ሚካኤል ኃያል ሚካኤል ከጠላታችን ነፃ አወጣን ከአምላክ ተልኮ እረዳን፤ (2) በፈተና ጊዜ ፈጥነህ ድርሰሃል ሀዘንን መከራን ከእኛ አርቀሀል እንዘምራለን ለታላቁ ክብርህ ታጋሽ እና ብርቱ ግሩም መልአክ ሚካኤል ኃያል ሚካኤል ከጠላታችን ነፃ አወጣን ከአምላክ ተልኮ እረዳን፤ (2) ሳጥናኤል ከክብሩ ትዕቢቱ ቢሽረው ሚካኤል ተሾመ ዘወትር ይኖራል በሚፈሩት ዙሪያ ዘወትር ይኖራል ከዲያቢሎስ ውጊያ ሕዝቡን ይታደጋል ሚካኤል ኃያል ሚካኤል ከጠላታችን ነፃ አወጣን ከአምላክ ተልኮ እረዳን፤ (፪)