ወዳጄ ሆይ እነሆ ውብ ነሽ የታተመች ፈሳሽ እንከን የሌለሽ የተዘጋች መቅደስ ንጽሕት አዳራሽ ሕዝቅኤል ያየሽ የምሥራቋ በር ማንም ያልገባባት ከአምላክ በስተቀር የልዑል ማደሪያ አማናዊት መቅደስ ስለ ንጽህናሽ ምስጋናን እናድርስ ሁለቱንም የሆንሽ እናትና ድንግል ማህደረ መለኮት ወላዲተ ቃል ያለ ዘርአ ብእሲ በኅቱም ድንግልና አምላክን የወለድሽ ሐመልማለ ሲና ምሥራቀ ምሥራቃት ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ ጨረቃን የምትመስይ ፀሐይን የወለድሽ የማለዳ ብርሃን ለዐይን የምታሳሺ ጽዮን እናቴ ሆይ ከጎኔ አትሽሺ