እመቤታችን ባንቺ ምልጃ (2) ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ (2) መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና (2) ለጌታችን ተአምር----በማየ ቃና ተመርጣ ታድላ---በማየ ቃና መጀመሪያ ሆነች-----በማየ ቃና ቃና ዘገሊላ----በማየ ቃና ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ሥፍራ የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ እመቤታችን ባንቺ ምልጃ (2) ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ (2) መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና (፪) ታውቋት ስላለችው----በማየ ቃና ወይንኬ አልቦሙ----በማየ ቃና ውኃ ወይን ሲሆን----በማየ ቃና ሁሉ አዩ ሰሙ----በማየ ቃና ቃናን ሊያዳርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ሥፍራ የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ እመቤታችን ባንቺ ምልጃ (2) ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ (2) መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና (፪) አሳላፊዎቹ----በማየ ቃና ግራ ቢገባቸው----በማየ ቃና የድንግል ማርያም ልጅ----በማየ ቃና ከጭንቅ አወጣቸው----በማየ ቃና ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ሥፍራ የድንግልም ክብር ተገለጠ የምልጃ ሥራ እመቤታችን ባንቺ ምልጃ (2) ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ (2) መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና (፪) እኛም እናምናለን----በማየ ቃና ተስፋ ትንብልና----በማየ ቃና ስለ ቃልኪዳኗ----በማየ ቃና ሁሉ እንደሚቃና----በማየ ቃና ቃናን ሊያደርጋት የተአምሩ ቀዳሚ ሥፍራ የድንግልም ክብር ተገለጠ ይምልጃ ሥራ እመቤታችን ባንቺ ምልጃ (2) ድንግል ማርያም ባንቺ ምልጃ (2) መድኃኔዓለም ተአምር ሠራ በማየ ቃና (፪)