ማን እንደ እርሱ እንደ እግዚአብሔር ቸርነቱ ብዙ በሰማይ በምድር ሞገድና ነፋስ የሚታዘዙለት አብርሕት ቀላያት የመሰከሩለት ኅቱም መቃብር ሳይከፍት የተነሳ ነፍሳትን ያዳነ ከሲዖል አበሳ ፈዋሴ ድውያን ቸርነቱ ብዙ የጸጋ ልብሳቸው ጽድቅን ለታረዙ የተዋረዱትን ከፍ ከፍ የሚያረግ ለባልቴቷ ዳኛ ፈራጅ ለደኃ አደግ የጠፋውን አዳም ሊፈልግ የመጣ ከባርነት አለም ከፅልመት ያወጣ ብርሃን ዘበአማን ጨለማን ያራቀ ሰውን ከራሱ ጋር ሞቶ ያስታረቀ በመከራ ሳሉ ሕዝቦቹን ያሰበ ሥጋውና ደሙን ቆርሶ የመገበ ከባቴ አበሳ ምሕረቱ የበዛ ጌታችን እርሱ ነው የሁላችን ቤዛ