እመ አምላክ እመ አምላክ አስቢኝ በሠርክ እመ አምላክ እመ አምላክ አስቢኝ በሠርክ አዝ--------------------// ሐዘኔ ጭንቀቴ በጣም በዛብኝ ከልዸሽ አስታርቂኝ አንቺው አማልጂኝ ከመንበሩ ቆመሽ ንገሪው ለልጂሽ እናቱነሽና እርሱ አያሳፍርሽ አዝ--------------------// እኔ ኃጢያተኛው በደሌን አውቃለሁ ምርኩዜ ነሽና እከተልሻለሁ መንገዱ ጠፍቶብኝ የጽድቁ ጐዳና መብራቱን አብሪልኝ እመጣለሁና አዝ--------------------// መመገብ ይቅርብኝ አልራብና ስምሽን ስጠራ እጠግባለሁና አበው ሊቃውንቱ በአንቺ ይመካሉ እመአምላክ እያሉ ስምሽን ይጠራሉ አዝ--------------------// ከገሃነም አውጪኝ ከዚያ ነበልባል ከሲኦል ወድቄ እንዳልቃጠል ያ የስቃይ ሃገር ባሕሩ ያሰምጠኛል አንቺ ከለመንሽው ልጅሽ ያዝንልኛል አዝ--------------------// እኔስ እፈራለሁ ምግባሬን ሳየው ደካማው እምነቴ እየለኝ ነው አልረሳሽም ድንግል እማፀንሻለሁ አማላጅነትሽ መድህን ነው አውቃለሁ እመ አምላክ /2/ አስቢኝ በሠርክ