አምላክ ለኛ ብሎ ቃል ኪዳን የሰጣት(፪) የሰዎች አማላጅ ኪዳነ ምህረት ናት(፪) ከአንቺ በተገኘው በቅዱሱ ፍሬ(፪) ዓለም ተቀድሷል ይኸውና ዛሬ(፪) ካህናት በከበሮ ሲያመሰግኑሽ(፪) እኛም በጭብጨባ እንዘምርልሽ(፪) እንደ አማለድሽው በላዔ ሰብን(፪) እኛንም እባክሽ አደራ አማልጅን(፪) ስምሽ ግርማ ያለው ኪዳነ ምህረት የኃጥአን አማላጅ የጌታዬ እናት(፪)