ኦ ሚካኤል /2/ ሊቀ መላእክት በኃጢአት እንዳንወድቅ እንዳንሞት ፈጥነህ ተራዳን አጽናን በእምነት /2/ ለያእቆብ ነገድ ሚካኤል ለእስራኤል " ጠባቂያቸው ነህ " መልአከ ኃይል " ፍቅርን አድለን ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት /2/ ነጸብራቃዊ ሚካኤል ተክህኖ ልብስ " ሐመልማለ ወርቅ " ዓይኑ ዘርግብ " ፍቅርን አድለን ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት /2/ በስእልህ ፊት ሚካኤል እቆማለሁ " ፈጥነህ ተራዳኝ " አለሁ በለኝ " ፍቅርን አድለን ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል የእኛ አባት /2/