ቅዱስ ሚካኤል /3/ ነፍሴ ሲጨነቅ ሲዝል ሥጋዬ ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ አንተ ስለሆንክ ሚካኤል የአምላክ ባለሟል " ልመናን ፈጥኖ " ከአምላክ ያቀርባል " የዋኅ መልአክ ነህ አዛኝ ለሰው ምልጃህ ፈጣን ነው ለምናምነው /2/ ደዌ የጸናበት ሚካኤል በአንተ ይድናል " በአደባባይህ " ምስክር ሆኗል " ከቤቱ መጥቶ የተማጸነ በቃልኪዳንህ ሕይወቱ ዳነ /2/ ከአምላክ ተሰጥቶህ ሚካኤል ክብርህ ያበራል " ለጎስቋላው ሰው " መጠጊያ ሆኗል " ትልቅ ትንሹ ደሃው ሀብ ሙ ለምኖ አግኝቷል ከአምላክ በስሙ /2/ በብሉይ ኪዳን ሚካኤል ከአምላክ ተልከህ " ህዝበ እስራኤልን " ነጻ ያወጣህ " በአዲስ ኪዳንም ድንቅ ሥራ አለህ በተአምራትህ ትፈውሳለህ /2/ ባለ መድኃኒት ሚካኤል ያቃተውን " ፈዋሽ ጠበልህ " ሆኖኛል ኃይል " እንደ መጻጉ ድኅነት አገኘን ፈውሰኸናል በአንተ ተመኝን /2/