ተቅበዝብዘን ነበር ነፍሳችን ቆዝማ እንጠፋ ነበረ በሲኦል ጨለማ ሁሉም አዘንብሎ ለጥፋት ሲቃረብ አወጣን እየሱስ ከዲያብሎስ መረብ ደም ግባት የለውም ሰለኛ ተገርፏል ይህንን ህማሙን ማንሰውኮ አምኖዋል በእውነት ደዌያችን እርሱ ተቀበለ እርቃኑን ተሰቅሎ ቀራኒዮ ዋለ! ተጨነቀ ጌታ ተሰቃየ ጌታ በመስቀል ሞተ ሞትን ጠላትን ሊረታ እንደሚታረድ በግ በሸላቾቹ ፊት ዝምታን መረጠ እንዲያሲያገላቱት ደም ግባት የለውም ሰለኛ ተገርፏል ይህንን ህማሙን ማንሰውኮ አምኖዋል በእውነት ደዌያችን እርሱ ተቀበለ እርቃኑን ተሰቅሎ ቀራኒዮ ዋለ! አፉን አልከፈተም ሲሰድቡት ሲከሱት ሐሞትና ከርቤ ቀላቅለው ሲያጠጡት አለም ጭካኔዋን ብታፈራርቅም ከይቅርታ ሌላ አልመለሰላትም ደም ግባት የለውም ሰለኛ ተገርፏል ይህንን ህማሙን ማንሰውኮ አምኖዋል በእውነት ደዌያችን እርሱ ተቀበለ እርቃኑን ተሰቅሎ ቀራኒዮ ዋለ! ደዌ ማይስማማው በስጋው ታመመ የዓለምን ጠቢባን በዚህ አስገረመ ሞቱ ግርፋቱ ሲያስቡት ይገርማል ዓለም የፈጠረ በፍጡራን ታስሯል ደም ግባት የለውም ሰለኛ ተገርፏል ይህንን ህማሙን ማንሰውኮ አምኖዋል በእውነት ደዌያችን እርሱ ተቀበለ እርቃኑን ተሰቅሎ ቀራኒዮ ዋለ! ምን አይነት መውደድ ነው ምን አይነት ትዕግስት ሰውን ያፈቀረ የፍጥረት አባት ምን አይነት ርህራሄ ምን አይነት ይቅርታ በመስቀል ተሰዋ የፍጥረታት ጌታ በመስቀል ተሰዋ በፍጥረታት ፋንታ ደም ግባት የለውም ሰለኛ ተገርፏል ይህንን ህማሙን ማንሰውኮ አምኖዋል በእውነት ደዌያችን እርሱ ተቀበለ እርቃኑን ተሰቅሎ ቀራኒዮ ዋለ!