ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም ረዳቴ እርሱ ነው በመከራዬ ቀን /2/ ሐዘኔ እጅግ በዝቶ ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ ሳይኖር ከስደቴ ዘመን ሰላም ከእኔ ርቆ ከሚካኤል በቀር ጭንቀት አስጠብቦኝ በዙሪያዬ ከቦኝ ዛሬ ግን አጽናኜ ከሚካኤል በቀር ሚካኤል ደረሰ ጠላቴ አፈረልኝ ሚካኤል ነው የዳዊት ረዳት ከጎልያድ ያዳነው ሚካኤል ነው መንፈሳዊ ብርታት ኃይልንም የሠጠው /2/ አዝ --- ቃልኪዳኑ ግሩም ከሚካኤል በቀር ዝክሩን ለዘከሩት ሥሙንም ለጠሩት አጋንንት አይቀርቡም ከሚካኤል በቀር ሥእሉ ባለበት ድርሳኑን ቢ=ደግሙት በረከት ይገኛል ከሚካኤል በቀር እርሱን ሲማጽኑት ከለመኑት በእውነት ሚካኤል ነው በትረ መስቀል ይካ የሚጠብቀኝ ሚካኤል ነው ከአንበሶች መንጋጋ የሚ ደገኝ /2/ አዝ --- በኑሮአችን ሁሉ ከሚካኤል በቀር እርሱ ይመራናል እርሱ ይረዳናል ፈርሑ<ንን ድል ነስቶ ከሚካኤል በቀር ከግብጽ አውጥቶናል በብርሃን መርቶናል የኤርትራን ባሕር ከሚካኤል በቀር ከፍሎ እንዳሻገረን ከነዓን ገብተናል ሚካኤል ነው ከበልዓም እርግማን እስራኤልን ያዳነው ሚካኤል ነው ዛሬም በአዲስ ኪዳን ክብሩ የገነነው /፪/