ዘካርያስ ርእየ ተቅዋመ ማኅቶት ኩለንተሃ ወርቅ በየማና ወበጸጋማ አእጹቀ ዘይት/2/ ነቢያት ይትፌሥሑ ሐዋርያት ይትሐሰዮ በውስቴታ ወዳዊት ይዜምር በውስተ ማኅፈዲሀ /2/ ትርጉም፡- በቀኟም በግራዋም የዘይት ጫፍ ያላት የመብራት መቅረዝ ዘካርያስ አየ ነቢያትና ሐዋርያት በውስጧ ደስ ይላቸዋል ዳዊትም በውስጧ ያመሰግናል