ኀበ ቀራንዮ ደብረ መድኃኒት ቀራንዮ (2) ኀበ ቀራንዮ የመስቀሉ ቃል ለእኛ የእግዚአብሔር ኃይል ነው /2/ ለማያምኑት ሞኝነት ነው ለእኛ ግን ሕይወት ነው /2/ እንመሰክራለን ፈጣሪያችን አለ እንመሰክራለን አማኑኤል አለ እንመነው አንካደው ፈጣሪያችን ቸር ነው /2/ እንመሰክራለን ድንግል አማላጅ ናት እንመሰክራለን ማርያም አማላጅ ናት እንመናት አንካዳት የአማኑኤል እናት ናት /2/ ኀበ ጥበባት ኀበ ልሳናት /4/ ዮሐንስ /2/ ወንጌለ ስብከት /፪/