መስቀል አበባ ውብ አበባ አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ መስቀል አበባ ተቀብሮ ሲኖር አደይ አበባ ሥነ ስቅለቱ መስቀል አበባ እሌኒ አገኘች አደይ አበባ ደገኛይቱ መስቀል አበባ ውብ አበባ አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ መስቀል አበባ ጥራጊ ሞልተው አደይ አበባ አይሁድ በክፋት መስቀል አበባ ጢሱ ሰገደ አደይ አበባ መስቀሉ ካለበት መስቀል አበባ ውብ አበባ አደይ አበባ ነሽ ውብ አበባ መስቀል አበባ ወንዙ ጅረቱ አደይ አበባ ሸለቆ ዱሩ መስቀል አበባ አሸብርቀው ደምቀው አደይ አበባ ላንተ መሰከሩ