በምን /2/ እንመስላት ድንግል ማርያም/2/ ምሳሌ የላትም /2/ ክብሯን የሚመጥን/2/ የሙሴ ጽላት ነሽ የምሕረት ቃል ኪዳን የያእቆብ መሰላል የአብርሃም ድንኳን የብርሃን መውጫ የኖኅ ድንቅ መርከብ የመላእክት እኅት የርኅሩኃን ርግብ/2/ የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር የእዝራ መስንቆ የጌድዮን ፀምር ድንግል እመቤት ናት የጻድቃን በር ሆና የተገኘች የአምላክ ማኅደር/2/ የቅዱሳን እናት የዓለም ንግሥት ችላ ተሸከመች መለኮት እሳት ብርሃን ትሁነን ጨላማን ገላልጣ አማልዳ ታስምረን ከዚህ ዓለም ጣጣ/2/