ዕፀ መስቀል የክብር መውረሻ ሰይጣንን ድል መንሻ የክብር ባለቤት ዕፀ መስቀል የተሠዋበት ዕፀ መስቀል ዕፀ መስቀሉ ነው ዕፀ መስቀል የዓለም መድኃኒት ዕፀ መስቀል አዝ . . . እንደ እሌኒ ንግሥት ዕፀ መስቀል ፍጹም አክብራችሁ ዕፀ መስቀል ሁላችሁ ገስግሱ ዕፀ መስቀል መስቀሉን ይዛችሁ ዕፀ መስቀል አዝ . . . ያለ ኃይለ መስቀል ዕፀ መስቀል የሰላም ዓርማችን ዕፀ መስቀል ሊሸነፍ አይችልም ዕፀ መስቀል ሰይጣን ጠላችን ዕፀ መስቀል አዝ . . . እሳተ መለኮት ዕፀ መስቀል ያላቃጠለው ዕፀ መስቀል ሰይጣንን የሚያነድ ዕፀ መስቀል ዕፀ መስቀሉ ነው ዕፀ መስቀል አዝ . . . እንደተባረከው ዕፀ መስቀል ቆስጠንጢኖስ ንጉሥ ዕፀ መስቀል በመስቀል ብርሃን ዕፀ መስቀል ወደ እውነት እንገስግስ ዕፀ መስቀል አዝ . . . የተዋሕዶ ልጆች ዕፀ መስቀል ገሥግሡ በተስፋ ዕፀ መስቀል ዕፀ መስቀል ያዙ ዕፀ መስቀል ጠላት እንዲጠፋ ዕፀ መስቀል አዝ . . .