colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

የዓለምን በደል

የዓለምን በደል የሰውን ግፍ አይቶ ዘጠና ዘጠኙን መላእክት ትቶ ጽድቅን ለመፈጸም በደልን አጥፍቶ የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ የሰማያት ሰማይ የማይችሉት ንጉሥ ተወልዶ ሲጠመቅ እኛን ለመቀደስ ተራሮች ደንግጠው ዘለሉ እንደ ፈረስ የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ ባህር ተጨነቀች ጠበባት መሬቱ ዮርዳኖስም ሸሸ አልቆመም ከፊቱ እንደተናገረው ዳዊት በትንቢቱ የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ ልጁ በዮርዳኖስ ጽድቀን ሲመሠርት መጣ በደመና ሰማያዊው አባት እየመሰከረ የልጁን ጌትነት የሰላሙ መሪ የሰላሙ ዳኛ አምላክ ተወለደ ተጠመቀ ለኛ