ሃሌ ሃሌ ሉያ /2/ በሰማይ በምድር ምሕረት ሆኗልና ሃሌ ሃሌ ሉያ አሜን ሃሌ ሉያ መላእክት ዘመሩ አመሰገኑት እየተደነቁ በአምላክ ቸርነት/2/ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት አሉ እረኞችም አብረው እሱን አከበሩ/2/ አዝ ----------- ዓለምን ለመፍጠር ከተጠበበበት ይበልጣል ከሁሉም እኛን ያዳነበት /2/ ከዳግማዊት ሔዋን ከእመቤታችን በረቂቅ ጥበቡ ተወልዶ አዳነን/2/ አዝ --------------- ሁላችሁም ሂዱ ከቤተልሔም ታገኙታላችሁ በከብቶች ግርግም ኢየሱስ ክርስቶስ ወሀቤ ሰላም ሞታችንን ወስዶ ሕይወትን ሰጠን/2/ አዝ ---------- ወልደ እግዚአብሔር መጣ ከላይ ከሰማይ ፍቅር አወረደው ከመንበሩ ላይ /2/ አልተጸየፈውም መሆን ከግርግም ትኅትናው ደነቀኝ የመድኃኔዓለም /2/ አዝ ------