ግነዩ ለእግዚአብሔር እስመ ሔር/2/ አዝ-------------- እናመስግናሽ የአምላክ እናት በዝማሬ /2/ የዓለም ቤዛ ነውና የማኅፀንሽ ፍሬ/4/ አዝ ----------- ከሰማየ ሰማያት ወርዶ ከአንቺ ተወልዶ /2/ መለኮት ወረደ ዮርዳኖስ እኛን ለመቀደስ /4/ አዝ ----------- በድንግልና የወለድሽው ክርስቶስ/2/ የድኩማኖች ብርታት ነው የሕሙማን ፈውስ/4/ አዝ ------------ በዮሐንስ እጅ ተጠመቀ እዳችንን ፋቀ/2/ በቸርነቱ ጠብቆ ከበደል አራቀን/4/ አዝ ------------- ስምሽን የጠራ ዝክርሽንም የዘከረ/2/ ቅድስት ቅዱሳን ማርያም ድንግል አንቺ ነሽ/2/ አዝ ---- እመቤታችን እናታችን ማርያም/2/ የተማጸነሽ ይድናል ለዘለዓለም/4/ አዝ ---- ድንልናሽ ሳይለወጥ ወልድን የወለድሽ የጌታችን እናት ማርያም ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ የጌታችን እናት ማርያም ንጽሕት ሆይ አንቺ ነሽ ድንግልናሽ ሳይለወጥ ወልድን የወለድሽ /፳/ የጌታችን እናት ማርያም ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ የጌታችን እናት ማርያም ንጽሕት ሆይ አንቺ ነሽ