ሰማይና ምድር የማይወስኑትን ተወስኖ አየነው በጠባብ ደረት ዘጠና ዘጠኙን መላእክትን ትቶ አገኘነው ዛሬ በበረት ተኝቶ አዝ ------------ የጥበብ ሰዎች መጡ/2/ ሰምተውት በዜና /2/ እያበራላቸው ኮከብ እንደፋና /2/ አዝ ----- ድንግል እመቤቴ ሰላምታ ይድረስሽ ለአምላክ ወገኖች መመኪያቸው የሆንሽ ከአንቺ ተወለደ የዓለም መድኅን ኩነኔን አጥፍቶ ጽድቅን ሊያወርሰን አዝ --------------------- ጌታችን ሲወለድ በቤተልሔም ሐዘን ተደምስሶ ሰፈነ ሰላም እንጨቶች አፈሩ ፍሬ በረከት ወንዞች ሁሉ ሆኑ ማርና ወተት አዝ --------------------- ሰብአ ሰገል መጡ ሊሰግዱ በሙሉ የእስራኤል ንጉሥ ወደ የት አለ እያሉ እጅ መንሻውን ሰጡት እንደየሥርዓቱ እጣኑን ለክህነት ወርቁን ለመንግሥቱ አዝ ---------------------