ማርያም/3/ ደስ ይበልሽ በገብርኤል ሰላምታ/2/ ባንቺ ስላደረ የዓለም ሁሉ ጌታ /2/ አዝ -------------- የአምላክ ቸርነቱ ፈቃዱ ሲሆን ጨለማው ተገፎ ሲወጣ ብርሃን አዝ -------------------- ድንግል ተቀምጣ በቤተ መቅደስ ሐር ወር አስማምታ ስትፈትል ንግሥት አዝ ------------------ ገብርኤል /2/ ዜናዊ ሐዲስ የአምላክን መወለድ ሥጋ በመልበስ አዝ --------------- ገብርኤል ሲያበስራት ድንግል ስትሰማ በእርስዋ ላይ አደረ የመለኮት ግርማ አዝ -------- እውነተኛ መልአክ መሆኑን ስላየች ይሁንልኝ ብላ ቃሉን ተቀበለች