ከነቢያት ሀገር ኢየሩሳሌም ከቅድስት አውራጃ በቤተልሔም በጎል ተወለደ/2/ መድኃኔዓለም/2/ አዝ----- ለእኛ ቤዛ ሊሆን በበደልነው ፈንታ ዛሬ ተወለደ ይገባል እልልታ/2/ አዝ --------------------- የነግሥታት ንጉሥ የነዳያን ሕይወት ተጠቅልሎ ተኛ በጎለ እንስሳ አዝ --------------------- ትኅትናን ሊያስተምር በሕፃንነት በከብቶች ማደሪያ ተኛ በበረት አዝ --------------------- ግኡዛን የሆኑ የማይናገሩ እስትንፋሳቸውን እንስሳት ገበሩ