ተወለደ አምላክ ተወለደ አዝ -------- አንዲት ብላቴና የአሥራ አምስት ዓመት ልጅ ጌታን ወለደችው በመላእክት አዋጅ በኅቱም ድንግልና ተወለደ ጌታ ዓለምን የሚድን የሰዎች አለኝታ አዝ-------------- ይህ ዓለም በቃሉ ከተፈጠረበት ይበልጣል ልደቱ አምላክ ሰው የሆነበት እንደምን ይገርማል ይሄ ተዋሕዶ አየነው አምላክን ከድንግል ተወልዶ አዝ ----------------- ፍጹም ድንግልና ክብርን የተመላሽ እንደምን አምላክን በማሕፀን ያዝሽ ዓለምን በቃሉ የፈጠረ ጌታ ወለደችው ድንግል የሔዋን አለኝታ አዝ -------------------- አንቺ ብላቴና እናታችን ማርያም በምድር ተፈልጎ እንደአንቺ አልተገኘም በሐሰብ በግብር ንጹሕ ስለሆነች ለአምላክ ማደሪያ ድንግል ተመረጠች