ድንግል /2/ ወላዲተ ቃል/2/ አሟሟትሽ በጥር ነሐሴ መቃብር ድንግል የአንቺስ ለብቻ ነው ትንሣኤሽ ሲነገር ድንግል ሥጋሽ በምድር ላይ የታለ እንደ ፍጡር አርጓል ወደ ሰማይ ከክርስቶስ መንበር አዝ -------- ሥጋሽን ሲያሳርጉ መላእክት በሰማይ ቶማስ በደመና ሲመጣ መንገድ ላይ ድንግል መግነዝ ተቀበለ ለሐዋርያት ሊያሳይ ድንግል አዝ ---------- ትንሣኤሽን ሽተው ግራ ሲገባቸው ድንግል ሐዋርያት ጾመው ተገለጥልሻላቸው ድንግል ተቀብራ አልቀረችው በምድር ከደጇ ድንግል ወደላይ አረገች እሷም እንደልጇ ድንግል አዝ ------- ለማየት ሲጓጉ የድንግልን ትንሣኤ ድንግል እርገቷን አወቁ በብዙ ሱባኤ ድንግል እኛም እንጸልይ ደጃችን እንዝጋ ድንግል ከወላዲተ አምላክ እንድናገኝ ዋጋ ድንግል