እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር አልቦ ነገር /፫/ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር መካኒቱን ወላድ አንተ ታደርጋለህ ከጭንጫ ዐለት ላይ ውኃን ታፈልቃለህ በወጀብ መካከል አንተ መንገድ አለህ የአስጨናቂዎችን ክንድ ትሰብራለህ እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር አልቦ ነገር /፫/ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር ለሶምሶን ብርታቱን የሰጠኸው ፅናት በጠላቶቹ ፊት ሞገስ የሆንክለት የእጅህን በረከት ከአርያም ላክልኝ ፊትህን አብራልኝ እኔም እድናለሁኝ እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር አልቦ ነገር /፫/ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር የኤርትራ ባሕር ከፊት ተዘርግቶ የፈርኦን ሠራዊት ከኋላቸው መጥቶ ዋይታ ሲበረታ ሙሴን ተናገርከው ባሕር ተከፈለ ሕዝቡን አሻገርከው እስመ አልቦ ነገር ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር አልቦ ነገር /፫/ ዘይሰዓኖ ለእግዚአብሔር ሰማያት ደመናን ከቶ ባይቋጥሩ ከብቶችም ከበረት ከጋጣ ባይኖሩ ሸለቆን በውኃ ቤትን በበረከት መሙላት ያውቅበታል የዘለዓለም አባት