colormap #003366#336699#3366CC#003399#000099#0000CC#000066#006666#006699#0099CC#0066CC#0033CC#0000FF#3333FF#333399#669999#009999#33CCCC#00CCFF#0099FF#0066FF#3366FF#3333CC#666699#339966#00CC99#00FFCC#00FFFF#33CCFF#3399FF#6699FF#6666FF#6600FF#6600CC#339933#00CC66#00FF99#66FFCC#66FFFF#66CCFF#99CCFF#9999FF#9966FF#9933FF#9900FF#006600#00CC00#00FF00#66FF99#99FFCC#CCFFFF#CCCCFF#CC99FF#CC66FF#CC33FF#CC00FF#9900CC#003300#009933#33CC33#66FF66#99FF99#CCFFCC#FFFFFF#FFCCFF#FF99FF#FF66FF#FF00FF#CC00CC#660066#336600#009900#66FF33#99FF66#CCFF99#FFFFCC#FFCCCC#FF99CC#FF66CC#FF33CC#CC0099#993399#333300#669900#99FF33#CCFF66#FFFF99#FFCC99#FF9999#FF6699#FF3399#CC3399#990099#666633#99CC00#CCFF33#FFFF66#FFCC66#FF9966#FF6666#FF0066#CC6699#993366#999966#CCCC00#FFFF00#FFCC00#FF9933#FF6600#FF5050#CC0066#660033#996633#CC9900#FF9900#CC6600#FF3300#FF0000#CC0000#990033#663300#996600#CC3300#993300#990000#800000#993333

ድንቅ ነው በጣም

ድንቅ ነው በጣም ድንቅ ነው /2/ በሠርጋችሁ እለት ተገኘ መድኃኔዓለም በሠርጋችሁ እለት ተገኘች ድንግል ማርያም በቃልህ ተመርተው ለዚህ ቀን በቅተዋል በፊትህ ጋብቻን ይኸው ፈጽመዋል በፈሰሰው ደምህ ኅብረት መስርተዋል በሥጋም በነፍስም /2/የአንተ ነን ብለዋል አዝ --- ከአዳም አንድ አጥንት ከጐኑ ወስደህ አጋር እንድትሆነው ሔዋንን ሰጠህ ሁለቱንም ባርከህ እንደፈጠርካቸው ዛሬም ለሙሽሮች/2/ ሰላምን ስጣቸው አዝ --- ጌታ ሆይ በሕግህ በቃልህ መሠረት አንድ ሆነዋልና በዚህ ቅዱስ እለት እርሱንም እሷንም ባርከህ ቀድሳቸው ዘለዓለማዊ ፍቅር /2/ ጽናትን ስጣቸው አዝ --- የዲያቢሎስ ተንኮል እንዳያስታቸው እስከ መጨረሻው ጋሻ ሁንላቸው ከቅድስቲቷ ቤት ሁለቱም ሳይርቁ ጽናቱን ስጣቸው /2/ አብረው እንዲዘልቁ